ETHIOPIAN WOMEN'S ALLIANCE IN VICTORIA

የኢትዮጵያ ሴቶች ሕብረት በቪክቶሪያ

ስለ እኛ

የኢትዮጵያ ሴቶች ህብረት በቪችቶሪያ(ዐWዓቭ) በ ፳፩፮ አ።ም ተመሰረተ።መስራች እማዬነሽ ስዩም ተመሳሳይ ሃሳብ ካላችው ሴቶች ኢትዮጵያን ጋር በመሆን የቋንቋ፤ የብሄር ፤ እና የሃይማኖት ብዝሃነት ባለው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በግል ወይንም በቤተሰብ ደረጃ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ውስብስብ ችግሮችን ለመቅረፍ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ተገነዘቡ። መስራቾቹ በአንድ ብሄር፤ ቋንቋ ወይንም የሃይማኖት ቡድን ላይ ከማተኮር ከሴቶች ጋር ተባብሮ በመስራት የኢትዮጵያ ማህበረስብን ችግሮች በአጠቃላይ መፍታት መጀመር የተሻለ ዉጤት ያመጣል ብለው ያምናሉ።የኢትዮጵያ ሴቶች ህብረት በቪክቶሪያ እያደገ ሲመጣ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት ያላችው አባላት ተቀላቅለውታል። የአባላቱም ትኩረት የኢትዮጵያ ሴቶች በአዲሱ ሃገራችው እስኪደላደሉ ስራ እየሰሩ ኢትዮጵያውያን አውስትራልያን ልጆችን ሲያሳድጉ እና እንደማህበረሰብ ሲገነቡ ድጋፍ መስጠትና ማብቃት።

በቪክቶሪያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊና ትውልድኢትዮጵያዊን ሴቶች እና ወጣቶች በማደራጀት እና በመደገፍ ሙሉ አቅማቸውን:እንዲጠቀሙ: ማስቻል::
ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች ጋር በመስራት ሴቶችን ማብቃት እና ጠንካራ እና የተባበረ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ መፍጠር::
  • አክብሮት ከተለያየ ቋንቋ:ሃይማኖት እና ባህል ካላቸው ኅብረተሰብ የሚመጡትን ሁሉ ሴቶች ማክበር::
  • ሴቶችን ማብቃት በቪክቶሪያ የሚኖሩ ከተለያየ ማኅብረተሰብ የሆኑ ሴቶች በግልም በጋራ ማብቃት::
  • እምነት በምንረዳቸው እና በምንደግፋቸው ሰዎች በአባሎቻችን ውስጥ እና በባልደረቦች እና በማህበረሰቦች ውስጥ እምነት ማሳደር::
  • ግልጽነት በምንሰራቸው ስራዎተች ሁሉ ለህብረተሰቡ እና የገንዘብ ደጋፊዎቻችን ተጠያቂነት እና ግልጽኝነት ማስፈን::.

የእኛ ሥራ

የእናቶች፣ የቤተሰብ ቀን በዓል በማክበር በማህበራዊና ጤና ጉዳዮች ላይ ያለንን ግንዛቤ ለማሳደግ እንደ መድረክ የሚያገለግለን ቁልፍ ሁነት ነው። እናም በቅርቡ ካካሄዳቸው ሥራዎችና እንቅስቃሴዎች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል።

  • በጋራ እንቅስቃሴን ማድረግ ፡ የስፖርትን ከፍተኛ ኃይል ለወጣቱ ለማስገንዘብና በአልኮልና ዕፅ ሳቢያ የሚከሰት ጉዳትን ለመከላከል በአልኮልና ዕፅ ፋውንዴሽን፣ ከማሪብሮንግ ከተማ እንዲሁም ከልሎች የማህበረሰብ አገልግሎትና ማህበራት ጋር በመተባበር እየሠራን እንገኛለን።
  • በወጣቶች የአእምሮ ጤንነት ላይ የሚያተኩሩ ትምህርታዊ ሴሚናሮችን ለመስጠት ሙያተኞችን በመጋበዝ ውጤታማ ሥራን ለመስራት ችለናል። ለምሳሌ ያህልም 2017 ፕሮፌሰር ፓትሪክ ማጓሪን በመጋበዝ በወጣቶች የአእምሮና ጉጂ ባህርያት ላይ ሴሚናር የተሰጠ ሲሆን ይህም በትውልዶች መካከል የሚኖር ክፍተት ፤ በወጣቱ የአእምሮ ጤንነት ከዚህም ድጋፍ ከየት እንሚገኝ አጉልቶ በማሳየት ረገድ ጠቃሚነቱ የማያጠያይቅ ነበር።
  • በቤተሰብ ብጥብጥ እና በልጆች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የፓናል ውይይት ተጀመረ።
  • ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ማህበረሰብ በተወሰኑ ጤናማ ባልሆኑ ግንኙነቶች መንስኤ ላይ የሚያተኩሩ የማህበረሰብ ዌብናር ሴሚናሮች።
  •  
  • አዲስ የመጡትን እና ጥገኝነት ፈላጊዎችን ጨምሮ በማኅበረሰባችን ውስጥ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በገንዘብ ማሰባሰብ ተነሳሽነት እና ከዋናው አገልግሎቶች እና ከማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር በማገናኘት ድጋፍ አድርገናል።

በቅርቡ እንገናኝ የሚል የ YouTube ሰርጥ ተከታታዮች ጀምረናል። በዚህ ፕሮግራም ከማህበረሰቡ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች እና ተግዳሮቶች ላይ እንወያያለን። ስለ ተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ያላቸውን ግንዛቤ ለመወያየት እና ባህላዊ ቅርሶቻቸውን እና ማንነታቸውን ለማክበር ልጆችን ጨምሮ የማህበረሰብ አባላትን ቃለ መጠይቅ እናደርጋለን።

  • በቪክቶሪያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ብቸኝነትን እና ማግለልን ለመቀነስ በ COVID-19 ወረርሽኝ ወቅት የማህበረሰብ ግንኙነቶችን እና ተሳትፎን (በዙም በኩል) ፈጥረናል።
  • በ COVID-19 ወረርሽኝ ወቅት የአእምሮ ደህንነት አስፈላጊነት ግንዛቤን እዲጨምሩ አድርገናል
  • የተተረጎሙ የኮቪድ -19 ዝማኔዎችን እና መረጃዎችን በአማርኛ አቅርበናል

ክስተቶች

Comments Box SVG iconsUsed for the like, share, comment, and reaction icons

ምንም መጪ ክስተቶች የሉም

የድርጅታችንን ወቅታዊ ሁኔታ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለዉን ቅፅ ይሙሉ ።

የኛ ቡድን

Emma-Seyoum-Tegegn

Emma Seyoum-Tegegn

Founder and President

Tsigreda Mekonnen

Vice President

Helen Taye Abebe

Treasurer

Hanna Tadesse

Secretary

Meskerem Tadesse

Executive Committee Member

Meron Tesfaye Gebrehiwot

Social Media Coordinator